ቫሴክቶሚ (vasectomy) ምንድን ነው?
ቫሴክቶሚ የወንድ ዘር ማሰትላለፊያ ቱቦ በመቋጠር የሚሰራ ዘላቂ እና ቋሚ የሆነ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ ነው።
ቫሴክቶሚ ወደፊት ልጅ መውለድ እንደማይፈልጉ እርግጠኛ ለሆኑ ወንዶች ወይም ጥንዶች ተስማሚ የእርግዝና መከላከያ አማራጭ ነው።
ቫሴክቶሚ ሀኪሞን ካማከሩ በኋላ በማንኛውም ሰዓት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሊሰራ የሚችል ህክምና/ፕሮሲጀር ነው።
ቫሴክቶሚ ወደፊት ልጅ መውለድ እንደማይፈልጉ እርግጠኛ ለሆኑ ወንዶች ወይም ጥንዶች አስተማማኝ እና ውጤታማ የእርግዝና መከላከያ አማራጭ ነው።
-
- ቫሴክቶሚ እርግዝናን በመከላከል ረገድ ወደ 100% የሚጠጋ ውጤታማ ነው።
- ቫሴክቶሚ በተመላላሽ ክፍል የሚሰራ ፕሮሲጀር/ህክምና ሲሆን የጎንዮሽ ጉዳት የማስከተል እድሉ አነስተኛ ነው።
- ቫሴክቶሚ ወንዶች በስነተዋልዶ ጤና እና በቤተሰብ እቅድ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚያስችል አማራጭ ነው።

ወንዶች እንዴት የስነተዋልዶ ጤና ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ይችላሉ?
በተዋለዶ ጤና የወንዶች ተሳትፎ ማለት! አባቶች/ወንዶች ማህበረሰብ ፣ እናቶች ፣ ሴቶችና ፣ ቤተሰባቸው የተሻለ የተዋልዶ ጤና አገልግሎት አቅርቦት እንዲኖራቸው በመንከባከብና በመደገፍ የመላውን የቤተሰብ ጤናና ደህንነት ማስጠበቅ ነው ፡፡
ወንዶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከታች በተዘረዘሩት ሶስት ዋና ዋና የተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች ላይ ለራሳቸው፤ ለቤተሰባቸውና ለህብረተሰብ ጤናና ደህንነት ጠቀሜታ በፍላጎት መሳተፍ ይችላሉ!!
-
- በቀጥታ የአገልግሎት ተጠቃሚ በመሆን/ደንበኛ/ የቤተሰብ እቅድ/ቫሴክቶሚ/ተጠቃሚ በመሆን
- ለባለቤታቸው/ለቤተሰባቸው አጋር በመሆን ለቤተሰባቸው አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ በማድረግ
- የተዋልዶ ጤና አገልግሎት የለውጥ ሐዋሪያ በመሆን እንደ ደጋፊ/አጋዥ/ ጠበቃ/ ሆነው አገልግሎቱን ለህብረተሰብ በማስተማርና በማስተዋወቅ ተጠቃሚ እንዲሆን ይረዳሉ
ቫሴክቶሚ (Vasectomy)
%
የስኬት መጠን አለው
የተሳሳቱ አመለካከቶች እና እውነታዎች
ቫሴክቶሚ በፆታ ግንኙነት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል?
ቫሴክቶሚ በጾታ ስሜት ወይም በግብረ ሰጋ ግንኙነት ላይ ምንም አይነት ተጽዕኖ አያሳድርም።
ቫሴክቶሚ የወንድ መራቢያ አካልን ይጎዳል?
ቫሴክቶሚ የወንድ መራቢያ አካልን በመተው የዘር ፍሬ ማስተላለፊያ ቱቦን ብቻ በመቋጠር የሚሰራ ነው።
ቫሴክቶሚ ከባድ የህመም ስሜት ይኖረዋል?
ቫሴክቶሚ እንደተሰራ መጠነኛ የሆነ የህመም ስሜት ሊኖረው ይችላል ነገር ግን ህመም ሰሜት ከጨመረ ሃኪሞን በማማከር ማስታገሻ መድሃኒት ማግኘት ይቻላል።
ቫሴክቶሚ (vasectomy) የት ማሰራት ይቻላል?

ፀደይ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ
ስልክ: 0112737370

ምቹ ክሊኒክ
ስልክ: 0713073507
ባለሞያዎቻችን

ዶ/ር አስቻለው ስዩም
የቤተሰብ ዕቅድ ባለሙያ